ወቅታዊ ሁኔታዎች
ተጨማሪስለ ቤተ ክርስቲያናችን
ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅድሳትን እንሸጣለን
ለክርስትና ሥርዓት የሚሞላ ቅጽ
የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ
በብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልያስ ገብረእግዚአብሔር አሳሳቢነትና ጥረት ቤተክርስቲያናችንን በማሳደግና አገልግሎቷን በማስፋት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሰባሰቡባት፤ ትምሕርት የሚቀስሙበትና ሃይማኖታቸውን የሚያጠነክሩበት ተቋም እንድትሆን በደብሩ ምዕመናን የተቋቀቋመ
ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ሐዋርያት ሰማዕታትና ቅዱሳን አበው በብዙ ተጋድሎና ድካም እስካሁን ያቆይዋትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ቀጣይነት የሚያረጋግጠው በየዘመኑ የሚነሳው ትውልድ እምነቱንና ሥርዓቱን ተረካቢ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው::
በፈቃደ እግዚአብሔር በ 1995 እ.አ.አ የተመሰረተው የኦስሎ ቅ/ገብርኤልና የአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 20 አመታት በኪራይ ቤቶች በመጠቀም አቅሙ የፈቀደውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለምእመናን እየሰጠ ያለ ሲሆን ፤ነገር ግን የራሱ ቤተክርስቲያን ባለመኖሩ አገልግሎቱን በተፈለገው መጠን ማሳደግ አልተቻለም:: ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ምንም መሥራት የማይቻል መሆኑን ህዝበ ክርስቲያኑ አውቆትና ተረድቶት ከከንቱ ውዳሴ ርቆ፣ በአንድ ልቡና፣ በሙሉ ፈቃደኝነት፣ በአስተዋይነት እና በታዛዥነት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመስራት ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን፡፡