የሕንፃ ኮሚቴ

ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ሐዋርያት ሰማዕታትና ቅዱሳን አበው በብዙ ተጋድሎና ድካም እስካሁን ያቆይዋትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ቀጣይነት የሚያረጋግጠው በየዘመኑ የሚነሳው ትውልድ እምነቱንና ሥርዓቱን ተረካቢ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው::

ቤተ ክርስቲያን ስንል ክርስትያኖች ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኙበት የተመረጡት ክርስትያኖች ቤታቸውን ለጾሎት ቤት አድርገው የሚጠቀሙበት ቤት አንደሆነ በሐዋርያት ሥራ ም.፭፮ ቁ.፯ የተገለጸ አና በሐዋርይት ሥራ ም.፳ ቁ.፪፰ መሰርረት ክርስቶስ በደሙ የገዛቸው የክርስቶስ አካሉ የሆነች ቤተክርስቲያን መስራት አና መገልገል አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን የተገነዘበችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ አሀጉራት አብያተ ቤተ ክርስቲያን እያነፀች ተከታዮቿን ስትጥብቅ የቆየችዉ። በዚህም መሰረት በፈቃደ እግዚአብሔር በ 1995 እ.አ.አ የተመሰረተው የኦስሎ ቅ/ገብርኤልና የአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 20 አመታት በኪራይ ቤቶች በመጠቀም አቅሙ
የፈቀደውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለምእመናን እየሰጠ ያለ ሲሆን ፤ነገር ግን የራሱ ቤተክርስቲያን ባለመኖሩ አገልግሎቱን በተፈለገው መጠን ማሳደግ አልተቻለም:: ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ምንም መሥራት የማይቻል መሆኑን ህዝበ ክርስቲያኑ አውቆትና ተረድቶት ከከንቱ ውዳሴ ርቆ፣ በአንድ ልቡና፣ በሙሉ ፈቃደኝነት፣ በአስተዋይነት እና በታዛዥነት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመስራት ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን፡፡ በኖርዌይ የኦስሎ ቅ/ገብርኤልና የአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የቦታ ችግር ለመቅረፍ እና የራስዎ የሆነ ህንጻ ቤተክርስቲያን እንዲኖራት የደብሩ ጠቅላላ ጉባኤና የቤተክርስቲያኑ የበላይ ጠባቂ በብጹዕ አባታችን አቡነ ኤሊያስ ገብረእግዚአብሔር የታመነበት ሲሆን ህንጻ ቤተክርስቲያኑን ለመስራትም ሆነ ለመግዛት በሃላፊነት የሚሰራ በቃለ አዋዲዉ ደንብ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 18 በሚያዘዉ መሰረት ከምዕመን በጠቅላላ ጉባኤዉ የተመረጠ የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል። በኖርዌይ ኦስሎ ቅ/ገብርኤልና የአቡነ ተክለሐይማኖት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሥር የምንኖር ኢትዮጵያውያን በብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልያስ ገብረእግዚአብሔር አሳሳቢነትና ጥረት ቤተክርስቲያናችንን በማሳደግና አገልግሎቷን በማስፋት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሰባሰቡባት፤ ትምሕርት የሚቀስሙበትና ሃይማኖታቸውን የሚያጠነክሩበት ተቋም እንድትሆን በደብሩ ምዕመናን የተቋቀቋመ ኮሚቴ ነዉ ።

ይህም ኮሚቴ የሚሰራዉን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሥርዓት ባለዉ መንገድ ለማካሄድ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለዉ አሰራር እንዲኖር፣ ያደርጋል::

የቤተክርስቲያን ሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ. እግዛብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!