በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እ/አ/አ/ በ1995 ዓ/ም የተመሠረተችው በኖርዌይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 20 ዓመታት በኪራይ ቤቶች በመጠቀም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መንፈሳዊ አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች። ነገር ግን የራሷ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ባለመኖሩ አገልግሎቱን በተፈለገው መጠን ማሳደግ አልተቻለም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ በጠቅላላ ጉባኤውና በአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ ገብረ እግዚአብሔር ስለታመነበት በቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 18 መሠረት ስምንት አባላት ያሉት የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ/ም (ማርች 22 ቀን 2013 እ/አ/አ/) ተቋቁሟል። የኮሚቴው ዓላማ የምእመናንን ብዛትና የኖርዌይን የአየር ጠባይ የሚመጥን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መገንባት ወይም መግዛት ነው።
የመጀመሪያው ደረጃ የኮሚቴው ሥራ ያተኮረው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ወይም ለመገንባት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጥናት ላይ ነው። ይህም ለሁለተኛውና ለዋናው ሥራ መሠረትና ምሰሶ ሆኗል። በዚህ ስር የተከናወኑት አበይት ክንውኖች የሚከተሉት ናቸው።
-
ሕዝበ ክርስቲያኑ ስለሚገነባው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በቂ ዕውቀት እንዲጨብጥና ጽኑ አቋም እንዲኖረው ተደርጓል
-
ከኖርዌይ አብያተ ክርስቲያናት፣ ከመንግስትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አጥጋቢ ግንኙነት ተመስርቷል
-
የተቀናጁና ውጤታማ የገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብሮች ተካሂደዋል
-
ግልጽና ተጠያቂነት ያለው የገንዘብ አሰባሰብ ሥርዓት ተዘርግቷል
-
የኮሚቴው ሥራ ግልጽና አሳታፊ እንዲሆን ተደርጓል
-
አሁን የምንገለገልበት የማዮሽቱዋ ቤተ ክርስቲያን እንድንገባና በምንፈልገው ሁኔታ እንድንጠቀምበት ተደርጓል
-
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ወይም ለመገንባት የሚያስችል የጥናትና የዲዛይን እቅድ ተሠርቷል
-
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከባንክ በምን መልኩና ምን ያህል ብድር ማግኘት እንደሚቻል ተጠንቷል
የሁለተኛው ደረጃ የኮሚቴው ሥራ ያተኮረው ደግሞ የሚሸጥ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ወይም ቦታ ማፈላለግ ላይ ነው። በኢንተርኔት ለሽያጭ የሚወጡ ቦታዎችን በመከታተልና ባዶ ቦታዎችን እንዲሁም ሕንፃዎችን በአካል በመጎብኘትና በማጥናት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። በተለይም የፕሮጀክትና ምህንድስናና የአማራጭ መንገዶች ክፍሎች ሙሉ ኃይላቸውን ያስተባበሩት በዚህ ሥራ ላይ ነው። በዚህ በሁለተኛው የሥራ ደረጃ የተከናወኑ ሌሎች ሥራዎች ቀጥለው የተዘረዘሩት ናቸው።
-
ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት ቦታ ይሰጠን ዘንድ ለኦስሎ ማዘጋጃ ቤት በተፃፈው ደብዳቤ መሠረት ቢሮው ኦስሎ ውስጥ ለሃይማኖት ተቋማት ግንባታ ሊውሉ የሚችሉ ባዶ ቦታዎችን አጥንቶ ሁለት ቦታዎችን አግኝቷል። ዳሩ ግን መጨረሻ ላይ ቦታዎችን መንግስት ለልማት እንደሚፈልጋቸው አሳውቋል።
-
ቋሚ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የምናገኝበት መንገድ እንዲመቻችልን ለሺርክሊ ፌለስሮድና ለኦስሎ ጳጳስ ቢሮ ጥያቄ ቀርቧል ይህ በቀጣይነት የሚከናወን ነው
-
ይህን ጉዳይ ለመፈጸም ታላላቅ የውይይትና የምክክር ጉባኤዎች ከብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ኤልያስ፣ ከኦስሎ ጳጳስ፣ ከሺርክሊ ፌለስሮድ እንዲሁም ከልዩ ልዩ የሃይማኖትና የመንግስት ተቋማት ተወካዮች ጋር ተካሂደዋል ለቀጣይ ሥራዎች መሠረት ሆነዋል
-
ልዩና አዋጭ የሆኑ ዘዴዎችን አጥንቶ በ2017 በሥራ ላይ እያዋለ ይገኛል
ባጠቃላይ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ሥራውን የሚያከናውነው በተለያዩ ክፍሎች ስር በሚያገለግሉ ምእመናን ነው። በኮሚቴው ስር የሚገኙ የአገልግሎት ክፍሎችና አበይት ተግባራት እንዲሁም የአገልጋዮች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ባጭሩ ተገልጿል። ዳሩ ግን የአገልጋዮች ብዛት እንደ ሥራው ስፋትና ጥልቀት እየታየ ሊጨምር ይችላል። ሁሉም ክፍሎች ሪፖርት የሚያደርጉት ስምንት አባላት ላሉት ለዐቢይ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ነው። ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ደግሞ ለሰበካ መንፈሳው አስተዳደር ጉባኤ፣ ለጠቅላላ ጉባኤና ለአህጉረ ስብከቱ በዓመት ሁለት ጊዜ ሪፖርት ያደርጋል።
ሠንጠረዥ 1: የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ክፍሎች፣ ዐበይት ተግባራት፣ አገልጋዮችና ሓላፊዎች
የአገልግሎት ክፍል |
አበይት ተግባራት |
አገልጋዮች |
የክፍል ሓላፊ |
ጽ/ቤት |
የኮሚቴውን ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢና ጸሐፊውን ያካተተ ክፍል ሲሆን አጠቃላይ የኮሚቴውን እቅድና የሥራ አፈፃፀም መምራት፣ መገምገም፣ የሰው ኃይል ማሟላት፣ ሪፖርት ማዘጋጀት ዋና ተግባራት ናቸው |
ተክሉ አባተ፣ ተዋሰን ተሾመ፣ ዳንኤል አበበ |
ተክሉ አባተ 93644054 |
ግንኙነት ክፍል |
ኮሚቴው የሚያደርጋቸውን የውስጥና የውጭ ግንኙነቶች መምራት፣ የኮሚቴውን ሥራ ለምእመናን ማሳወቅና ከምእመናን ግብዓት መሰብሰብ፣ አዋጭ ሃሳቦችን ማቅረብ |
ልዑል ዓለማየሁ፣ ጌዲዎን |
ልዐል ዓለማየሁ 91139611 |
ገቢ አሰባሳቢ |
የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከምእመናንና ከማናቸውም ግለሰቦችና ተቋማት ገቢ መሰብሰብ |
ሶስና ሀብተ ማርያም፣ ፍቅሩ ሁሴን፣ ጌታቸው በቀለ፣ ፋንታው ተሰማ |
ሶስና ሀብተ ማርያም 99479730 |
ሂሳብ ክፍል |
ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ መዘርጋት፣ ገቢና ወጪዎች በሥርዓትና በሕግ መፈጸማቸውን መቆጣጠርናሪፖርት ማድረግ |
ዳዊት ሻውል |
ዳዊት ሻውል 48354625 |
ገንዘብ ክፍል |
የኮሚቴውን ገቢዎች ተቀብሎ ወዲያውኑ ባንክ ማስገባትና በኮሚቴው የተወሰኑትን ወጪዎች ማድረግ |
ዘቢብ ካሳሁን |
ዘቢብ ካሳሁን 96988399 |
አማራጭ መንገዶች |
ከኖርዌይ ቤተ ክርስቲያንና ተመሳሳይ ተቋማት ጋር በመደራደር ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝባቸውን ዘዴዎች ማነፍነፍና መፈፀምና ለኮሚቴው ሪፖርት ማድረግ |
ሂሩት ገብረ ኪዳን፣ ልዑል መኮንን፣ ተዋሰን ተሾመ፣ ሶስና ሀብተ ማርያም፣ አንዳርጋቸው ስዩም፣ ዳንኤል አበበ፣ ተክሉ አባተ |
ሶስና ሀብተ ማርያም 99479730 |
ምህንድስና ክፍል |
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛትም ሆነ ለመገንባት የሚያስችሉ የምህንድስና ሥራዎችን ማቀድ፣ መፈፀምና ሪፖርት ማድረግ |
ታጠቅ ፍቃዱ፣ ዳንኤል ንጉሤ፣ ፋኑኤል ገብረ ኢየሱስ፣ ይስሃቅ በቀለ፣ ብሩክ ኃይሌ |
ይስሃቅ በቀለ 97592932 |
ፕሮጀክት ክፍል |
ለኮሚቴው ሥራ ግብዓት የሚያገለግሉ የዳሰሳ ጥናቶችን ማካሄድና የፖሊሲ መፍትሔ ሃሳቦችን ማቅረብ |
ዳዊት ሻውል፣ ማርታ ኃይሉ፣ መሠረት ታዬ |
ዳዊት ሻውል 48354625 |