በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በኖርዌይ የኢ/ኦ/ተዋሕዶ የመካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ ምእመናን በሙሉ

 በኮሮና ቫይረስ(Covid-19) ወረርሽኝ ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን ዝግ ሆና መቆየቷ የሚታወቅ ነው። ይሁን እንጂ ከግንቦት 7 ቀን 2020 ዓ.ም ጀምሮ የእምነት ተቋማት ተከፍተው እስከ 50 ሰው በቤተ ክርስቲያን መሰብሰብ እንዲችሉ ከኖርዌይ መንግስትና የህብረተሰ ጤና ኢንስቲትዩት መመሪያ ከቅድመ ጥንቃቄ ጋር ተሰጥቷል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ እየሰራ ነው። በመሆኑም ከፊታችን እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2020 ዓ.ም ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችን በከፊል አገልግሎት የምትሰጥ መሆኑን በደስታ እየገለጽን የተሟላ አገልግሎት እስኪጀመር እና የመንግስትን አዋጅ ሙሉ በሙሉ መተግበር እስክንችል ድረስ ክርስትና ለሚያስነሱ እና የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን ለሚቀበሉ ምዕመናን ብቻ ክፍት የሚሆን መሆኑን ከወዲሁ ማስገንዘብ እንወዳለን። ከላይ የተጠቀሱት ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመምጣታቸው በፊት ከኖርዌይ መንግስት የተሰጡትን አዋጆች እና ምክረ ሀሳቦች ማማላት ይኖርባቸዋል። ከነዚህም ውስጥ፡

  1. ለሰበካ አስተዳደር ጽ/ቤት በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች 980 75 044 ወይም 947 85 936 በመደወል መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
  2. ምዕመናን ቢያንስ የ 1 ሜትር ርቀት እንዲጠብቁ
  3. የህመም ምልክቶች (የራስ ምታት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ በተደጋጋሚ ማስነጠስ) ከታዩ ወደ ቤ/ክ መምጣት የተከለከለ ነው።
  4. በጤና ባለሞያ ወይም በመንግስት ለ14 ቀን ከቤት እንዳይወጡ(quarantine) ወይም ለብቻዎ እንዲገለሉ (isolation) ከተነገርዎት ወደ ቤተ ክርስቲያን መመጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
  5. የስኳር፣ የልብ፣ የአስም፣ የደም እና የመሳሰሉ ህመምተኞች ለበሽታው ተጋላጭ የመሆን እድሎ ስለሚጨምር ወደ ቤ/ክ እንዲመጡ አይመከርም።
  6. ቤ/ክ ምግብ ይዞ መምጣት እና በሕብረት መመገብ የተከለከለ ነው።
  7. ለሕፃናት እና ለታዳጊዎች የሚያስፈልጉ የጥንቃቄ ቅድመ ሁኔታዎች ስላልተሟሉ ወደ ቤ/ክ ከመምጣት እንዲቆጠቡ።
  8. ወደ ቤ/ክ በሚመጡበት ጊዜ በር ላይ በተዘጋጀው ሳኒታይዘር(Antibac) በውኃ እና በሳሙና መታጠብ።
  9. በሳል እና በማስነጠስ ጊዜ በመሐረብ/በሶፍት ወረቀት ካልሆነው በክርኖት አፍ እና አፍንጫዎ በሸፈን ይኖርቦታል።
  10. ማንኛውም ምእመን ሳይመዘገቡ እና የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደሩን አውንታዊ ምላሽ ሳያገኙ በስተቀር ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት የተከለከለ ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ፈቅዶ ቤተ ክርስቲያናችን መደበኛ አገልግሎት እስክትጀምር ድረስ እንደተለመደው የቀጥታ ስርጭት በቤተ ክርስትያናችን ፌስ ቡክ እና ዩትዩብ (Facbook & Youtube) የምናስተላልፍ መሆኑን እያሳሰብን ከኖርዌይ መንግስት እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡትን አዋጆች እና መመርያዎች እየተከታተልን የምናሳውቃችሁ መሆኑንም ከወዲሁ እንገልጻለን።

እግዚአብሔር አምላክ አገራችንን፣ ህዝቦችዋን እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

በኖርዌይ የመካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጽ/ቤት

ግንቦት 14 ቀን 2020 ዓ.ም ኦስሎ, ኖርዌይ